Elyas melka PART 2 top 10 points ክፍል 2 ስኤልያስ መልካ ያልተነገሩ 10 ነጥቦች official video 2020
Description
፡፡፡፡ ኤልያስ መልካ የሁላችንንም ሞት ሞተ ፡፡፡፡
የኢትዮጲያ ሙዚቃ አሽቃባጭ ዘራፊዎች ምንም የማይመለከታቸው ደላሎች እንዲሁም
አንዳንድ ህሊናቸውን የሸጡ አርቲስቶች ብቻ የተጠቀሙበት የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ከሆነ ከረመ
እዚህ አገር የተዘረጋው ሙዚቃዊ system ሙዚቀኛውን ያገለለ የተወሰኑ አካላትን ብቻ ያደለበ
ዘርፍ ሆኖ ሙዚቀኛውን ተመፅዋች አድርጐታል
ኤልያስ መልካ ይሄን ለብቻው የታገለ የተጋፈጠ ህይወቱን የሰዋ ብርቱ ጀግና ሙዚቀኛ ነው
ኤልያስ ብቻ ሳይሆን ሙሉጌታ አባተን ጨምሮ ሌሎች አያሌ ከአርቲስቱ ጀርባ በመሆን
ተአምራቸውን ያሳዩን ሰዎች ተዝናንተው ሳይኖሩ ጥሪት ሳይኖራቸው እንደሻማ ቀልጠው አለፉ
የቀረነው እኔና አንተስ ሙዚቀኛው
አሁን መጠላለፉ ይበቃል
የጎሪጥ መተያየቱን እንተውና
ኤልያስን ሁለተኛ ሞት እንዳይሞት እንታደገው ህብረት ሊኖረን ይገባል
በተለይ እኛ የሙዚቃ አቀናባሪዎች producers አሁን የራሳችን ማህበር ሊኖረን ይገባል ወደድክም ጠላህም መተባበር ያዋጣናል
የ ኤልያስ መልካ ሞት ከምርም የኛም ሞት ነው
፡ ፡ ኤልያስ መልካ የሁላችንንም ሞት ሞተ ፡ ፡
እግዚያብሄር ነፍስህን በአፀደ ገነት ያኑርልን
Comments